
በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሂዷል።
ደም ሲለግሱ ያገኘናቸዉ የጣርማበር ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደግአረገ አንዱአለም ደም መለገስ የሰዉን ህይወት የሚያድን ክቡር ተግባር ነዉ ብለዋል።
ደም በመለገስ በደም እጦት ምክነያት የሚሞቱ እናቶችን ህይወት መታደግ ከስራዎች ሁሉ የተሻለ ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ በመሆኑ ደም መለገስ የሚችል ሁሉ ሊለግስ ይገባል ሲሉም አቶ ደግአረገ ተናግረዋል።
አቶ ደግአረገ አያይዘዉም በዛሬዉ እለት 35ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
በልገሳዉ አመራሮች ፣የመንግስት ሰራተኞችና ወጣቶች ተሳትፈዋል።




