
ጣወመኮ ነሀሴ 21/2017 ዓ.ም ደብረሲና
በስልጠናዉ የጣርማበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፓለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጥላሁን ታደሰ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መታገል ለተወሰነ አካል ብቻ የምንሰጠዉ ተግባር ሳይሆን የሁላችንም ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ሀብት ማስመዝገብ የሚጠበቅባቹህ አካላት በሙሉ ሀብትና ንብረታችሁን በማስመዝገብ ለሙስና ከሚያጋልጡ ሁነቶች መራቅ ይጠበቅባቹሀል ሲሉም አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የጣርማበር ወረዳ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ክፍል ለአዲስ ሀብት አስመዝጋቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
የጣርማበር ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተክለስላሴ ሰይፈ በበኩላቸዉ ባልተገባ መንገድ ሀብት በማካበት በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚደረግ ማንኛዉም እንቅስቃሴ ሙስና በመሆኑ በተገቢዉ መንገድ ያገኘነዉን ሀብት በማስመዝገብ ሙስናን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት የበኩላችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል።
የክፍሉ ባለሙያ አቶ ፈቃደ ደምሴ ስልጠናዉን ሰጥቷዋል።



