ማዕድ ማጋራት የፅድቅ መንገድና የህሊና እርካታ የሚያስገኝ ተግባር ነዉ።አቶ አለሙ የሺጥላ የጣርማበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ

በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን የማዕድ ማጋራትና የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ።
በድጋፉ የጣርማበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ የሺጥላ ማዕድ ማጋራት የፅድቅ መንገድና የህሊና እርካታ የሚያስገኝ ተግባር ነዉ ብለዋል።
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ በጎ ተግባራት ተከናዉነዋል ያሉት ሀላፊዉ የበረዳቸዉን ማልበስም ከበጎዎች የላቀ ተግባር ነዉ ብለዋል።
የጣርማበር ወረዳ ወጣትና ስፓርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በግዱ ወርቁ ከ124 በላይ ለሆኑ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያንን ማዕድ የማጋራትና የአልባሳት ድጋፍ የማድረግ ተግባር ተከናዉኗል ብለዋል።
ለማዕድ ማጋራቱ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ መደረጉንም አቶ በግዱ ተናግረዋል።
የጣርማበር ወረዳ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት ረድኤት ታዬ በበኩላቸዉ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተቸገሩ፣አረጋዊያንንና አቅመ ደካሞችን የመደገፍ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
ሀላፊዋ አያይዘዉም በዛሬዉ እለት የማዕድ ማጋራትና አልባሳት ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።
ፕሮግራሙን የወረዳዉ ወጣት ስፖርትና ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት አስተባብረዋል።





