
ጣወመኮ ነሀሴ 20/2017 ዓ.ም ደብረሲና
ድርጅቱ የመማሪያ ችግር ላለባቸዉ ተማሪዎች የሚሆን 2ሺህ 110 ደርዘን ደብተርና 5ሺህ 64 ዘመናዊ ቦርሳ ለወረዳዉ ጤና ፅ/ቤት አስረክቧል ሲሉ አቶ ደግአረገ አንዱአለም ተናግረዋል።
አቶ ደግአረገ አያይዘዉም ከደብተርና ቦርሳ በተጨማሪ ከ10ሺህ በላይ እስክርቢቶ፣ከ10ሺህ በላይ እርሳስ እንዲሁም ከ5ሺህ በላይ የእርሳስ ላፒስ ከድርጅቱ ድጋፍ ተደርጎልናል ብለዋል።
ድርጅቱ ያደረገዉን ድጋፍ ለችግረኛ ተማሪዎች እንዲያሰራጩ የጣርማበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ለወረዳዉ ትምህርት ፅ/ቤት አስረክቧል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ የፓለቲካ ዘርፍ ሀላፊዉ አቶ ጥላሁን ታደሰ አንድም ህፃን በትምህርት ቁሳቁስ ምክነያት ከትምህርት ገበታ ዉጭ እንዳይሆን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ብዙ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ተዘጋጅተል ብለዋል።


