
በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ በተለያዩ ምክነያቶች ተቋርጦ የነበረዉ የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ ስራ ተጀምሯል ሲሉ የወረዳዉ አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተክለስላሴ ሰይፈ ገልፀዋል።
እንደ ሀላፊዉ ገለፃ የወረዳ አስተዳደሩ የቢሮ እጥረትን ለመቅረፍ G+B4 የቢሮ ግንባታ አስጀምሮ ግንባታዉ በተለያዩ ምክነያቶች ተቋርጦ የቆዬ ቢሆንም አሁን ግንባታዉን መልሰን አስጀምረናል ብለዋል።
አቶ ተክለስላሴ አያይዘዉም በሰሜኑ ጦርነት፣ በዋጋ ግሽበትና በሌሎች ምክነያቶች ተቋርጦ የነበረዉን የቢሮ ግንባታ መልሶ ለማስጀመር ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዉ ስራዉ እንዲጀመር የወረዳዉ አስተባባሪ አመራር በቁርጠኝነት ግንባታዉ እንዲጀመር አድርገዋል ብለዋል።
ግንባታዉ ተጠናቆ ለአገልግሎት እስኪበቃ ሁሉም የወረዳችን ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ሰፊ ርብርብ እንድታደርጉ ሲሉም አቶ ተክለስላሴ መልዕክት አስተላልፈዋል።


