

የመስቀል በዓል ክርስቶስ ለሰዉ ልጆች የመጨረሻዉን ፍቅር የገለፀበት ነዉ። አቶ ሳሙኤል መርሻ የጣርማበር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
የጣርማበር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል መርሻ ለደመራና ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ጣወመኮ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ደብረሲና
የጣርማበር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል መርሻ ለመላዉ የወረዳችን ፣ከተማችንና ለመላዉ የኢትዮጲያ ህዝቦች ለ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪዉ በመልዕክታቸዉ መስቀል ክርስቶስ ለሰዉ ልጆች የመጨረሻዉን ፍቅር የገለፀበት በዓል ነዉ ብለዋል።
አቶ ሳሙኤል መስቀል ከፈተና በኃላ ድል፣ከጨለማ በኃላ ብርሀን ፣ከመዉደቅ በኃላ መነሳትን የሚያሳይ ታሪካዊ በዓል ነዉ ብለዋል።
መስቀል የጥላቻ ግድግዳ የፈረሰበት ፣ሰላምና እርቅ የሰፈነበት ፈጣሪ ደሙን አፍስሶ ስጋዉን ቆርሶ ህዝብና አህዛብን ያስታረቀበት በዓል ነዉ ሲሉም አቶ ሳሙኤል በመልዕክታቸዉ አስፍረዋል።
በዓሉ ከሀይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር ለኢትዮጲያ ህዝቦች ባህላዊ ቅርስና ዉርስም ነዉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪዉ መስቀል የብሩህ ተስፋና የብርሀን ምልክትም ነዉ ሲሉም ገልፀዋል።
በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመረዳዳት እንዲሁም በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል ሲሉም አቶ ሳሙኤል በመልዕክታቸዉ ገልፀዋል ።
በድጋሜ መልካም በዓል።
አቶ ሳሙኤል መርሻ የጣርማበር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ