
በጉብኝቱ የጣርማበር ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ዉብሸት ደበበን ጨምሮ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና የቋሚ ኮሚቴዉ አባላት ተሳትፈዋል።
በወረዳዉ እየተከናወኑ ያሉት የአስተዳደር ቢሮ፣የትምህርት ጽ/ቤትና ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ፣ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ቢሮ የፊኒሽንግና የመፀዳጃ ቤት እንዲሁም የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታዎች ሂደት ምልከታ ተደርጓል።
ግንባታዎቹ በጥራትና በታቀደላቸዉ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቁ መሰራት የሚገባቸዉን ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴዉ ገምግሟል።
በሂደት ላይ ያሉ ግንባታዎች በወቅቱ ተጠናቀዉ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መስራት እንደሚገባ በጉብኝቱ ተገልጿል።




