
ደብረ ሲና
ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
የጣርማበር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከጠቅላላ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ በዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ከሥራ አፈፃፀም ጋር ተያይዞ የታዩ ክፍተቶች ተገምግመዋል።
የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ተክለስላሴ ሰይፈ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ ተቋሙ የያዛቸውን ዕቅዶች ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልጸው፤ በየደረጃው የሚገኙ ሠራተኞች በየዘርፉ ያከናወኗቸው አበረታች ተግባራት ውጤታማ ነበሩ ብለዋል። በተለይም በበጀት ዓመቱ ውስጥ ከተከናወኑ አበይት ሥራዎች መካከል፣ በጽ/ቤቱ የሥራ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች የራሳቸውን ከፍተኛ ጥረትና ተነሳሽነት በመጠቀም ያሳዩት ለውጥና ያደረጉት ተሳትፎ ትልቅ ትኩረት የተሰጠውና ውጤታማ የነበረ መሆኑን አንስተዋል። ይህ በሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በልማት ሥራዎች ክትትል፣ በሪፖርት አደረጃጀትና በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የተመዘገበ ውጤት ለቀጣይ ሥራዎች ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑንም ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅት፣ በዓመቱ አፈፃፀም የታዩ ውስንነቶችን በመለየት ለቀጣዩ ዓመት የመፍትሔ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን፤ የ2019 በጀት ዓመት የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ የተገኙት ሠራተኞች በበኩላቸው፤ በቀጣይ ዓመት የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ጥራትና ቅልጥፍና በተሞላበት መንገድ ለማከናወን፣ የአሠራር ሥርዓቱን በማዘመንና የባለሙያዎችን አቅም በየጊዜው በመገንባት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
ጽ/ቤቱ በ2019 በጀት ዓመት በቀጣይ ሥራዎቹ ሁሉ የአሠራር ሥርዓቱን ይበልጥ በማዘመንና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ በመግለጽ የውይይት መድረኩ በስኬት ተጠናቋል


