
ደብረ ብርሃን፡ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አገልግሎት ሠጪ ፅህፈት ቤቶቹ በተበታተነ መልኩ የሚገኙና በአመት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ለኪራይ እያወጡ ነዉ።
በአሁኑ ወቅት በወረዳው ስር ከሚገኙ 27 የመንግሥት ጽሕፈት ቤቶች መካከል አምስቱ ተከራይተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ያሉት የወረዳ አስተዳደሩ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ተክለሥላሴ ሰይፈ ናቸዉ።
እነዚህን የጽሕፈት ቤቶች ክፍተቶች ለመሙላት እና ተበታትነው የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ስር ለማጠቃለል የሕንፃው ግንባታ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
በወረዳው ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ሰይፈ በበኩላቸው አስተዳደሩ ለአምስቱ ተቋማት ኪራይ ብቻ በየዓመቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ለማድረግ ይገደድ እንደነበር ጠቁመዋል።
በ2013 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ይህ ባለ አራት ወለል ሕንፃ በጸጥታ ችግር ምክኒያት ተቋርጧ ቢቆይም በአሁኑ ወቅት 65 በመቶ ያህሉ ሥራው መጠናቀቁ ተገልጿል።
ይህ ዘመናዊ ሕንፃ ሲጠናቀቅ ለጽሕፈት ቤቶች አገልግሎት ከሚሰጡ ክፍሎች በተጨማሪ የህፃናት ማቆያ እና የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) አገልግሎቶችን ባካተተ መልኩ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተገልጿል።
ለዓለም ለይኩን

